የሩሲያ የምግብ እርዳታ እንደ አውሮፓ ሕብረት ሳይሆን "ቀጥተኛና በፍጥነት የሚተገበር ነው" ሲሉ ተንታኙ ገለጹ
19:13 07.02.2026 (የተሻሻለ: 19:14 07.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ የምግብ እርዳታ እንደ አውሮፓ ሕብረት ሳይሆን "ቀጥተኛና በፍጥነት የሚተገበር ነው" ሲሉ ተንታኙ ገለጹ
የሩሲያ ማዳበሪያ እና ስንዴ መድረስ ለተወሰነ የኒጀር ህዝብ "የነበረውን ፍላጎት በአስቸኳይ የሚፈታ ነው" ሲሉ ኒጀራዊው የማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ተንታኝ ሞሃመዱ ጊምባ ሙርታላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
የ20 ሺህ ቶን ማዳበሪያ፣ 20 ሺህ ቶን ስንዴ እና 350 ቶን የሱፍ አበባ ዘይት ድጋፍ ከምንም በላይ "ተምሳሌታዊ ትርጉም ያለው ተግባር" መሆኑን ባለሙያው አጽንኦት ሰጥተዋል። ይህ እርዳታ ብቻውን የምግብ ዋስትና ችግርን ባይፈታም፣ የምግብ ዋጋ ግሽበትን በመቀነስ እና በቀታናው ያሉ ተያያዥ ስጋቶችን ለመከላከል ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግም አመልክተዋል።
ባለሙያው በተለይ፣ ይህ እርዳታ ከሌሎች እንደ አውሮፓ ሕብረት ካሉ አካላት እርዳታ በተለየ መልኩ "ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው" ነው ሲሉ ገልፀዋል። የአውሮፓ ሕብረት እርዳታ ብዙ ጊዜ በኒጀር ተቋማት ላይ የተለያዩ ፖሊሲዎችን ከመጫን እና ከቅድመ ሁኔታዎች ጋር እንደሚመጣም አክለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X