80 በመቶ ግንባታው የተጠናቀቀው የኬንያ ታሪካዊው ታላንታ ስታዲየም በሟቹ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሰየም ሩቶ ገለጹ
18:20 07.02.2026 (የተሻሻለ: 18:24 07.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
80 በመቶ ግንባታው የተጠናቀቀው የኬንያ ታሪካዊው ታላንታ ስታዲየም በሟቹ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሰየም ሩቶ ገለጹ
የስታዲየሙ ግንባታ ተጠናቆ በመጪው መጋቢት ወር ለርክክብ እንደሚበቃ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ ስታዲየሙ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመዘከር "የራይላ ኦዲንጋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም" ተብሎ እንደሚሰየም ይፋ አድርገዋል።
ፕሬዝዳንቱ የግንባታውን ሂደት የሚያሳይ ቪዲዮ ባጋሩበት ወቅት፣ "እነሱ በማታለልና በመጠራጠር ተጠምደው ነበር፣ እኛ ግን ሂደቱን አመንን... ይህ በጣም የሚያስገርም ነው፣ ትወዱታላችሁ" ብለዋል።
ዋና ዋና ዝርዝሮች፦
ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የሚገነባው ስታድየም ሲጠናቀቅ ለፈረስ ስፖርት፣ ለእግር ኳስ እና ለሌሎች ትልልቅ ዝግጅቶች የሚያገለግል የሀገሪቱ ትልቁ የስፖርት ማዕከል ይሆናል።
ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በቅርቡ የግንባታውን የጊዜ ሰሌዳና ቅንጅት ለመገምገም በስፍራው ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል።
ሩቶ ይህ ፕሮጀክት የስፖርት መሠረተ ልማትን ለማስፋፋት እና ለወጣቶች ዕድል ለመፍጠር ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X