የጌዴኦ ብሔር አዲስ ዓመት "ዳራሮ" በዲላ ከተማ ተከበረ
17:14 07.02.2026 (የተሻሻለ: 17:24 07.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የጌዴኦ ብሔር አዲስ ዓመት "ዳራሮ" በዲላ ከተማ ተከበረ
"ዳራሮ" ማኅበረሰቡ አዝመራ ተሰብስቦ ሲያበቃ በራሱ የጊዜ ቀመር መሠረት የአዲስ ዘመን መግባትን በማብሰር በብሩህ ተስፋ ተሞልቶ በድምቀት የሚያከብረው የምስጋና በዓል ነው።
"ዳራሮ" "መለምለም" ወይም "መጽደቅ" የሚል ፍቺ አለው፡፡ የተፈጥሮ ማንሰራራት፣ የቡቃያ ማፍራት እና የአዲስ ሕይወት ብስራት አስረጅ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
በዳራሮ በዓል አምስት የተለያዮ ሁነቶች ይከበራሉ እነርሱም ፋጭኤ፣ ሁሉቃ፣ ዳራሮ፣ አንድነትና የዓመቱ አዋጅ "ላላባ" ናቸው ሲል የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዓሉ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ለበዓሉ ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ ጌዴኦ ተወላጆች፣ የአጎራባች በሔረሰቦች ተወካዮችን ጨምሮ በርካቶች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፡፡
ከማሕበራዊ ሚዲያ የተገኘ ቪዲዮ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X