የኤፕስታይን ጥላ በምስራቅ አፍሪካ - አዲስ የወጡ ሰነዶች ቀጣናው የዓለም አቀፍ የሰዎች ዝውውር ቀለበት ኢላማ እንደነበር አጋለጡ
16:03 07.02.2026 (የተሻሻለ: 16:14 07.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኤፕስታይን ጥላ በምስራቅ አፍሪካ - አዲስ የወጡ ሰነዶች ቀጣናው የዓለም አቀፍ የሰዎች ዝውውር ቀለበት ኢላማ እንደነበር አጋለጡ
በአሜሪካ የጄፍሪ ኤፕስታይን ክስ ሂደት አዲስ ይፋ የሆኑ የወንጀል መዝገቦች፣ በርካታ የምስራቅ እና የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ከኤፕስታይን ዓለም አቀፍ የወሲብ ንግድ መረብ ጋር ግንኙነት ያላቸው ቦታዎች እንደነበሩ አመልክተዋል።
የአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ይፋ ካደረጋቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ገጾች መካከል፤ ኬንያ እና ሶማሊያ “ከህጻናት ወሲባዊ ጥቃት ተግባር” ጋር ተያያዥነት ያላቸው አካባቢዎች ተብለው የተለዩ ሲሆን፤ ታንዛኒያ እና ሴኔጋል ደግሞ በወንጀል መረቡ ውስጥ እንደ ማስተላለፊያ መስመር ማገልገላቸው ተገልጿል።
እነዚህ ሰነዶች በዓለማችን እጅግ አስነዋሪ ከሚባሉ ቅሌቶች አንዱ የሆነው የኤፕስታይን ጉዳይ አድማስ ምን ያህል ሰፊ እንደነበር የሚያሳዩ ሲሆን፤ መረቡ በአፍሪካ ውስጥ ስለነበረው ተሳትፎም አዳዲስ እና አሳሳቢ ጥያቄዎችን አስነስተዋል።
ሰነዶቹ ከቀጣናው ጋር ስላላቸው አስደናቂ ትስስር የሚያሳየውን ቪዲዮ ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X