በዛሬው ዕለት የተመረቀው የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት
14:27 07.02.2026 (የተሻሻለ: 14:34 07.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በዛሬው ዕለት የተመረቀው የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት
ሪዞርቱ የተገነባው በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ከሐይቅ ከተማ ሁለት ኪሎ ሜትር ራቅ ብሎ በሚገኘው ሎጎ ሐይቅ ላይ ነው፡፡
የገበታ ለትውልድ አካል የሆነው ፕሮጀክቱ፣ 16,700 ሜትር ስኩዌር መሬት ላይ ተንጣሏል፡፡
በተራሮች ለተከበው፣ ልዩ ልዩ የአእዋፍት ዝርያዎችን ለያዘው እና በ9ኛው ክፍለ ዘመን የተመሠረተው ዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ለሚገኝበት ሎጎ ሐይቅ አዲስ የጉብኝት እድል እንደሚከፍት ታምኖበታል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስት ዐቢይ አሕመድ በምረቃ ሥነ–ስርዓቱ ወቅት ያደረጉትን ሙሉ ንግግር በቪዲዮው ይመልከቱ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X