የአፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ በእያንዳንዱ ሀገር ደረጃ ሊገመገም ይገባል፤ በአኅጉር አቀፍ መታየት የለበትም - ደቡብ አፍሪካዊ ፕሮፌሰር
20:17 06.02.2026 (የተሻሻለ: 20:24 06.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ በእያንዳንዱ ሀገር ደረጃ ሊገመገም ይገባል፤ በአኅጉር አቀፍ መታየት የለበትም - ደቡብ አፍሪካዊ ፕሮፌሰር
"የኤስ ኤንድ ፒ" ትንበያ ያስቀመጠው የ4.5 በመቶ አማካይ የዕድገት መጠን እጅግ አስደናቂ እና አዎንታዊ ቢሆንም፣ የእያንዳንዱን አፍሪካ ሀገር ተጨባጭ ሁኔታ እንደማያንጸባርቅ ዳንኤል ሚየር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"አማካይ ማለት አንዱ እግር በፍሪጅ ውስጥ፣ ሌላኛው ደግሞ በምድጃ ውስጥ ሆኖ 'በአጠቃላይ ደህና ነኝ' እንደማለት ነው። ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም" ሲሉ አስረድተዋል።
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም፣ የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ለአፍሪካ ሀገራት የተሻለ ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው የገለጹት ሚየር፤ በአሁኑ ወቅት ጣራ የነካውን ከፍተኛ የወለድ መጠን በእጅጉ ሊቀንሱት እንደሚገባ አሳስበዋል።
"ይህንን የዕዳ ጫና ማስወገድ ከተቻለ ትልቅ እገዛ ይኖረዋል፤ ምክንያቱም ያንን ገንዘብ ለመሰረተ ልማት ግንባታ ማዋል እንችላለን" ሲሉ ተናጋሪው አጽንኦት ሰጥተዋል።
ይህም ሆኖ አፍሪካ በወጣት የህዝብ ቁጥር፣ በሰው ኃይል መጠን እና በሰፊ መሬቷ ትልቅ ጂኦፖለቲካዊ ጠቀሜታ አላት። በመሆኑም እንደ አሜሪካ፣ ሩሲያ እና ቻይና ያሉ ሀገራት ከአኅጉሪቱ ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ሚየር ገልጸዋል።
"ለመሰረተ ልማት ግንባታ፣ ለክህሎት ማበልጸጊያ እና እጅግ አስፈላጊ ለሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶች ብዙ እድሎች አሉ" ሲሉም አክለዋል።
የአፍሪካ ሀገራት ቀጣናዊ ተጋላጭነታቸውን እንዴት ማሸነፍ እንደሚችሉ ለማወቅ ቪዲዮውን ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X