የአዳማ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ባለፉት ስድስት ወራት 2.5 ቢሊየን ብር የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን አመረተ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአዳማ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ባለፉት ስድስት ወራት 2
የአዳማ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ባለፉት ስድስት ወራት 2 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.02.2026
ሰብስክራይብ

የአዳማ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ባለፉት ስድስት ወራት 2.5 ቢሊየን ብር የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን አመረተ

በልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ ውስጥ የሚገኙ 19ኙም ሼዶች በውጭና በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የተያዙ ሲሆን፤ ከ9 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠራቸውም የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በኢኮኖሚ ዞኑ ከሚመረቱ ምርቶች መሃከል፡-

ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣

የሕንጻና የብረት ቀለም፣

የኮንስትራክሽን ግብዓቶች፣

የመብራት ቆጣሪ እና

የሕጻናት ንጽህና መጠበቂያ ይገኙበታል፡፡

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት 3.4 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ ከቀናት በፊት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መናገራቸው ይታወሳል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0