ጤና ሚኒስቴር በሁሉም ሆስፒታሎች ክፍያዎች በዲጂታል መንገድ ብቻ እንዲፈፀሙ መወሰኑ ተዘገበ
19:16 06.02.2026 (የተሻሻለ: 19:24 06.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ጤና ሚኒስቴር በሁሉም ሆስፒታሎች ክፍያዎች በዲጂታል መንገድ ብቻ እንዲፈፀሙ መወሰኑ ተዘገበ
ይህ መመሪያ ሚኒስቴሩ፣ ባለፈው ዓመት ከበርካታ የፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢዎች ጋር በመተባበር ታካሚዎች በሞባይል ባንኪንግ እና በሌሎች የዲጂታል አማራጮች እንዲከፍሉ ያስጀመረውን ሥርዓት መሠረት ያደረገ ነው።
አላማውም የገቢ አሰባሰብ ግልጽነትን ለማረጋገጥ፣ የፋይናንስ ሪፖርቶችን ለማቀላጠፍ እና ለታካሚዎች ምቾትን ለመፍጠር ሲሆን፣ ከክፍያ በተጨማሪም የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለትን ከባህላዊ የወረቀት አሰራር ወደ ዲጂታል መቀየሩ ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅት የጤና ፋይናንስ ሥርዓቱ 52 በመቶ የሚሆነውን የተቋማቱን ወጪ የሚሸፍን ሲሆን፣ በዲጂታል ክፍያ አማካኝነት ይህንን ሽፋን ወደ 70 በመቶ ለማድረስ ታቅዷል ሲሉ የግል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
የዲጂታል እውቀቱ ለሌላቸው ወይም የገንዘብ እጥረት ላጋጠማቸው ተጠቃሚዎች ሌላ ቦታ ያለ ሰው በስማቸው ክፍያ እንዲፈጽምላቸው ማድረግ የሚችሉበት አሰራርም ተዘርግቷል ተብሏል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X