ኢትዮጵያ እና ብራዚል ንግድ እና ኢንቨስትመንትን የሚያሳደግ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

ሰብስክራይብ

  ኢትዮጵያ እና ብራዚል ንግድ እና ኢንቨስትመንትን የሚያሳደግ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

በዓለም አቀፍ ግንኙነት ረገድ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ የታመነበት ስምምነቱ፣ በኢትዮ-ብራዚል የኢኮኖሚ ትብብር ፎረም ላይ በይፋ ተፈርሟል፡፡

አጋርነቱ በሁለቱ የብሪክስ አባል ሀገራት መካከል የእውቀት ሽግግርን እና የፈጠራ አሰራሮችን በማስፋፋት፣ የኢኮኖሚ ትስስሩን እንደሚያጠናክር እና ልማትን እንደሚያፋጥን ይጠበቃል።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ስምምነቱ፣ "በደቡብ-ለደቡብ ትብብር እና በብሪክስ  የልማት መርሆዎች ላይ በጽኑ የተመሰረተ ነው" ሲሉ በፊርማው ሥነ-ሥርዓት ወቅት ተናግረዋል ስትል በስፍራው የተገኘችው የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ዘግባለች።

የብራዚል ግብርና ምርምር አስተዳደር ትብብር ፕሬዝዳንት ሲልቪያ ማሳሩሃ በበኩላቸው፣ "እዚህ እንድንገኝ ያደረገን ሳይንስ፣ ጽናት እና ፈጠራ ነው" ያሉ ሲሆን ብራዚል በግብርናው ዘርፍ ያስመዘገበችውን ውጤትና የቴክኖሎጂ እድገት ለአፍሪካ ሀገራት የማካፈል ፍላጎት እንዳላትም ገልጸዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0