አዲስ አበባ ባለፉት 6 ወራት 162.7 ቢሊዮን ብር በላይ የገቢ ግብር መሰብሰቧን ከንቲባዋ አስታወቁ
17:49 06.02.2026 (የተሻሻለ: 17:54 06.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አዲስ አበባ ባለፉት 6 ወራት 162.7 ቢሊዮን ብር በላይ የገቢ ግብር መሰብሰቧን ከንቲባዋ አስታወቁ
ይህም ከ2017 ጋር ሲነፃፀር 51.12 ቢሊዮን ብር ( 45.8%) የገቢ ጭማሪ ማሳየቱንም ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ለከተማዋ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ በአቀረቡት የ6 ወራት ሪፖርት ገልፀዋል፡፡
በ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር እቅድ አፈፃፀማ በአማካይ 95.3% ማሳካት መቻሉንም ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡ በዚህም በመንፈቅ ዓመቱ፦
በመንግሥት እና በግል አጋርነት ከ70 በላይ ፕሮጀክቶችን ወደ ሥራ ሲገቡ ከ1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ ካፒታል ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏል፡፡
በ4.9 ሚሊየን የሀገር ውስጥ እና 699 ሺህ 761 የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ጉብኝት 155 ቢሊየን ብር ወደ ኢኮኖሚ ፈሰስ ተደርጓል፡፡
በመንገድ መሠረተ ልማት (ግንባታና ጥገና) 708.34 ኪ.ሜ. ማከናወን ተችሏል፡፡
238 አዳዲስ ስትራቴጂክ ኢንዱስትሪዎች ተፈጥረዋል።
ተኪ ምርቶችን በማምረት 800.4 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል።
16,635 ቶን ምርት ለውጭ ገበያ ቀርቦ 123 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X