የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት ስድስት ወራት 52.26 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ
15:42 06.02.2026 (የተሻሻለ: 15:44 06.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት ስድስት ወራት 52.26 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ
ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከአዲስ ደንበኞች መስተንግዶ እና የማያገለግሉ ንብረቶችን በማስወገድ የዕቅዱን 96 ከመቶ ማስመዝገብ መቻሉን በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
266,916 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን እና ይህም ቁጥር ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ13.2 በመቶ ብልጫ እንዳለው አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጌቱ ገረመው አስታውቀዋል።
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከዋናው የኃይል ቋትና 47፣ ከፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች 16 በአጠቃላይ 63 የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ሥራ አስፈፃሚው በሰጡት መግለጫ ጠቁመዋል።
አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ባለፉት ወራት ከ52 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት የማሻሻያና መልሶ ግንባታ ሥራዎች መከናወናቸዉ ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X