"የኒው ስታርት" ስምምነት - ምን ይሸፍናል? ለምንስ ይገዳል?
"የኒው ስታርት" ስምምነት - ምን ይሸፍናል? ለምንስ ይገዳል?
የታሪካዊው "የኒው ስታርት" ስምምነት በሩሲያ እና አሜሪካ የስትራቴጂክ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ክምችት ላይ ገደብ የሚጥል የመጨረሻው ስምምነት ነው። ስምምነቱ ዛሬ፣ የካቲት 5 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ.) ያበቃል።
በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል ያለው የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ስምምነት ምን እንደሚገድብ ግልጽ መረጃው እነሆ፦
ስትራቴጂክ የጥቃት መሣሪያዎች፦ የኒውክሌር አረሮች እና እነሱን የሚያጓጉዙ የመተኮሻ ስርዓቶች።
የተቀመጡ ገደቦች፦
700 ዝግጁ የሆኑ የጦር መሣሪያ ማጓጓዣዎች፣
1,550 ዝግጁ የሆኑ የኒውክሌር አረሮች እና
800 ዝግጁ የሆኑ እና ያልሆኑ የጦር መሣሪያ ማስወንጨፊያዎች እና ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች።
ስምምነቱ የሚሸፍናቸው፦ አኅጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤሎች፣ ከባሕር ሰርጓጅ መርከብ የሚተኮሱ ሚሳኤሎች እና ግዙፍ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች።
የማያካትታቸው፦ ታክቲካዊ የኒውክሌር መሣሪያዎች፣ የሚሳኤል መከላከያ ስርዓቶች እና ሃይፐርሶኒክ መሣሪያዎች።
አጭር ታሪክ
▪ በጎርጎሮሳዊያኑ ሚያዝያ 8፣ 2010፦ በወቅቱ የሀገራቱ ፕሬዝዳንቶች ሜድቬዴቭ እና ኦባማ ተፈረመ።
▪እ.አ.አ. በ2018፦ ሁለቱም ወገኖች የተቀመጠውን ገደብ አሟሉ (ምንም እንኳን ሩሲያ አሜሪካ የምትከተለውን የማረጋገጫ ዘዴ ብትቃወምም)።
▪ እ.አ.አ. በ2021፦ በባይደን አስተዳደር ስር እስከ እስከ ጎርጎሮሳውያኑ የካቲት 2026 ድረስ ለተጨማሪ አምስት ዓመታት ተራዘመ።
▪ እ.አ.አ. በ2023 ፦ ሩሲያ አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገውን ድጋፍ እና የፍተሻ አለመግባባቶችን በመጥቀስ ተሳትፎዋን አገደች።
▪ እ.አ.አ. በ2025፦ ትራምፕ አዳዲስ ገደቦች እንዲቀመጡ እና ቻይናም በሂደቱ እንድትካተት ፍላጎት እንዳላቸው ተናገሩ።
▪ባለፈው መስከረም፦ ፑቲን፣ አሜሪካም ተመሳሳይ እርምጃ የምትወስድ ከሆነ፣ ስምምነቱ ካበቃ በኋላም ለተጨማሪ አንድ ዓመት ገደቦቹን ለማክበር ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ።
ዋና ዋና አለመግባባቶች
▫ ፍተሻዎች፦ በኮቪድ ምክንያት ተቋርጠው የነበሩት ፍተሻዎች፣ በኋላም በባንክ ማዕቀቦች እና በቪዛ ችግሮች ምክንያት ሳይቀጥሉ ቀርተዋል።
▫ የኔቶ የጦር መሳሪያ ክምችት፦ ሩሲያ በሚቀጥለው ማንኛውም ስምምነት የፈረንሳይ እና የብሪታንያ የኒውክሌር ኃይሎች እንዲካተቱ ትፈልጋለች።
▫ ቻይና፦ የአሜሪካ እና የሩሲያ የጦር መሣሪያ ክምችት ወደ እሷ ደረጃ (20 እጥፍ ያነሰ) ካልወረደ በስተቀር ስምምነቱን አልቀላቀልም ብላለች።
አሁን ያለንበት ሁኔታ
አሜሪካ፣ ለፑቲን የጎርጎሮሳውያኑ 2025 ጥያቄ እስካሁን ይፋዊ ምላሽ አልሰጠችም። የክሬምሊን ቃል አቀባይ ፔስኮቭ ሲያስጠነቅቁ፦ "ከጥቂት ቀናት በኋላ ዓለም ከዚህ ቀደም ከነበረው በበለጠ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ልትገኝ ትችላለች" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X