በደን ምርቶች የወጪ ንግድና በተኪ ምርቶች 14 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ተገኝቷል - የኢትዮጵያ ደን ልማት
20:31 05.02.2026 (የተሻሻለ: 20:34 05.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በደን ምርቶች የወጪ ንግድና በተኪ ምርቶች 14 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ተገኝቷል - የኢትዮጵያ ደን ልማት
ይህ ገቢ የተገኘው ከ3 ሺህ 248 ቶን በላይ የደን ምርት ወደ ውጭ በመላክና በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት በተሰራው ሥራ ነው ብሏል፡፡ ከዚህ ውስጥ ከ627 ሺህ ዶላር የሚልቀው "ከኤምዲኤፍ"፣ "ሃርድ ቦርድ"፣ "ፕለይውድ"፣ ፈርኒቸር ሞራሌ እና የአጠና ምርቶችን ወደ ውጪ በመላክ የተገኘ መሆኑን ተገልጿል።
በስድስት ወራት ውስጥ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ 1.15 ሚሊዮን ቶን የደን ውጤቶች ምርት ለማቅረብ በእቅድ ተይዞ ከ3 ሚሊዮን ቶን በላይ የደን ውጤቶች ምርት በማቅረብ አፈፃፀሙን ከፍ እንዳረገው በኢትዮጵያ ደን ልማት የደን ውጤቶች ስራ አስፈፃሚ ቢተው ሽባባው ተናግረዋል።
የሀገር ውስጥ የደን ምርት ውጤቶች ገበያ ተፈላጊነታቸው እያደገ በመምጣቱ ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የደን ምርት ውጤቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሬ እጥረትን መቀነስ መቻሉን ገልፀዋል ሲል ተቋሙ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X