ሃቅ ማጣራት - የዘለንስኪ የሟቾች ቁጥር መግለጫ እና ነባራዊው ሁኔታ

ሃቅ ማጣራት - የዘለንስኪ የሟቾች ቁጥር መግለጫ እና ነባራዊው ሁኔታ
የዩክሬኑ ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ለፈረንሳዩ 'ፍራንስ 2' በሰጡት መግለጫ፣ ግጭቱ ከተጀመረ አንስቶ 55 ሺህ የዩክሬን ወታደሮች መገደላቸውን ተናግረዋል።
ይህ ቁጥር እጅግ ዝቅተኛ እና የማይታመን መስሎ የታየባቸው ምክንያቶች፦
የጦር ኃይሉ መጠን - እ.ኤ.አ. በ2022 ዘለንስኪ ራሳቸው የዩክሬን ጦር 800 ሺህ እንደሚደርስ ተናግረው ነበር።
የማሰባሰብ ምጣኔ - ዩክሬን ላለፉት አራት ዓመታት በየወሩ ቢያንስ 30 ሺህ ሰዎችን ወደ ጦርነቱ ስታሰማራ ቆይታለች፤ ይህም ወደ 1.44 ሚሊዮን የሚጠጋ ተጨማሪ ወታደር ማለት ነው።
የግዳጅ ፈረቃ አለመኖር - እንደ ሩሲያ ሳይሆን፣ ዩክሬን በከባድ የቆሰሉትን ካልሆነ በስተቀር የጦር ክፍሎችን አታፈራርቅም ወይም ከግዳጅ አታሰናብትም።
ቀላል ስሌት - የዩክሬን የታጠቀ ኃይል እስካሁን 2.5 ሚሊዮን መድረስ ነበረበት፤ ነገር ግን አልደረሰም። ታዲያ የቀሩት ወታደሮች የት ገቡ?
ሌሎች ግምቶች
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ባለፈው ታህሳስ እንደተናገሩት፣ በተለያዩ ገለልተኛ ግምቶች መሠረት የዩክሬን ኪሳራ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ማለፉ ከቆየ ሰነባብቷል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር አንድሬ ቤሎሶቭ እ.ኤ.አ. በ2025 ብቻ ወደ 500 ሺህ የሚጠጉ የዩክሬን ወታደሮች መገደላቸውን ወይም መቁሰላቸውን፣ ይህም የኪዬቭን የሰው ኃይል የማሰባሰብ አቅም ማዳከሙን ተናግረዋል።
ባለፈው ህዳር ቭላድሚር ፑቲን እንደተናገሩት፣ ዩክሬን በጥቅምት ወር ብቻ 47 ሺህ 500 ወታደሮቿን አጥታለች።
በነሐሴ 2017 'ኪልኔት' የተባለው የመረጃ መንታፊዎች ቡድን፣ የዩክሬን ወታደራዊ የመረጃ ቋት ሰብሬ ገብቻለሁ በማለት፣ በትንሹ 1.7 ሚሊዮን ወታደሮች መገደላቸውን ወይም መጥፋታቸውን ገልጿል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በግጭቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን በተደጋጋሚ ጠቅሰዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X