ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ግርማው አበበ የተመድ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሳይንሳዊ አማካሪዎች አባል ሆኑ
19:48 05.02.2026 (የተሻሻለ: 19:54 05.02.2026)
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ግርማው አበበ የተመድ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሳይንሳዊ አማካሪዎች አባል ሆኑ
ድርጅቱ አዲስ ባቋቋመውና በዓለም የመጀመሪያው በሆነው "ገለልተኛ ዓለም አቀፍ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሳይንሳዊ ፓነል" ውስጥ የተካተቱት የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሳይንቲስቱ፣ የኢትዮጵያን ውክልና የሚያረጋግጡ ናቸው ተብሏል፡፡
በፓኔሉ ውስጥ ላይ ለሦስት ዓመታት የሚያገለግሉ ከዓለም ዙሪያ የተመረጡ 40 ባለሙያዎችን ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጥር 26 በነበረው የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አቅርበዋል፡፡
ይህ ፓነል የተመሠረተው እ.ኤ.አ በ2024 በተካሄደው የ"ሰሚት ኦፍ ዘ ፊዩቸር” ጉባኤ ላይ በጸደቀው "ዓለም አቀፍ የዲጂታል ስምምነት" መሠረት ነው፡፡
አንቶኒዮ ጉተሬዝ በ2025 ፓኔሉን ይፋ ባደረጉበት ወቅት፤ ዓለም የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ "ያላቸው" እና "የሌላቸው" ተብላ እንዳትከፈል በማስጠንቀቅ፣ የቴክኖሎጂው አስተዳደር ሁሉንም ያካተተ እና ፍትሐዊ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X