ኢትዮጵያ የሩስያ–አፍሪካ ጉባኤን ለማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የሩስያ–አፍሪካ ጉባኤን ለማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች
ኢትዮጵያ የሩስያ–አፍሪካ ጉባኤን ለማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.02.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የሩስያ–አፍሪካ ጉባኤን ለማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ በኢትዮጵያ የሩስያ ፌዴሬሽን አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ወቅት አምባሳደር ሃደራ ኢትዮጵያና ሩስያ የረጅም ጊዜ ዲፕሎማሲ ግንኙት ያላቸው እና ግንኙነቱም በኢኮኖሚያዊ ትብብርና በባለብዙወገን ግንኙነት መስክ እየተስፋፋ መምጣቱን ገልጸዋል።

አክለውም፣ ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱ ሁሉን አቀፍ የለውጥና የእድገት ሂደቶችን መነሻ በማድረግ የሩስያ-አፍሪካ ጉባኤን ለማዘጋጀት ያላትን ፍላጎት ጠቅሰው፣ የጉባኤውን ስኬታማነት ለማረጋገጥ በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።

በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን በበኩላቸው፣ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት በቅንጅት በመሥራት እያጠናከረች መሆኗን አንስተዋል።

ሁለቱ ወገኖች በአኅጉራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳብ ተለዋውጠዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የሩስያ–አፍሪካ ጉባኤን ለማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች
ኢትዮጵያ የሩስያ–አፍሪካ ጉባኤን ለማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.02.2026
አዳዲስ ዜናዎች
0