በዓለም ጤና ድርጅት መስፈርት መሠረት ሸካ ዞን ውስጥ ትራኮማ ከሕዝብ ጤና ስጋት ደረጃ መነሳቱን ተገለጸ
18:20 05.02.2026 (የተሻሻለ: 18:24 05.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በዓለም ጤና ድርጅት መስፈርት መሠረት ሸካ ዞን ውስጥ ትራኮማ ከሕዝብ ጤና ስጋት ደረጃ መነሳቱን ተገለጸ
በዞኑ ከጎርጎሮሳውያኑ 2019 ጀምሮ፣ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የፀረ-ባክቴሪያ መድኃኒቶች በማደል፣ ከ600 በላይ የዓይን ቀዶ ሕክምናዎች በማካሄድ በአጠቃላይ ከ250 ሺህ በላይ ሰዎችን ለዓይነ ሥውርነት ከሚዳርገው ቀዳሚ ተላላፊ በሽታ መታደግ መቻሉን ኦርቢስ አስታውቋል፡፡
ከጌዴኦ ዞን በመቀጠልም ይህን ግብ የተሳካበት ሁለተኛው የኢትዮጵያ ዞን ሆኗል።
በቀጣይም በስድስት ዞኖችና በ50 ወረዳዎች የዐይን ጤና ክብካቤን ለማጠናከር አዲስ መርሃ-ግብር እየቀረፀ እንደሚገኝ ተገልጿል። ይህም ለ3.3 ሚሊዮን ሕዝብ የዓይን ሞራ፣ የዕይታ ችግር ማስተካከያ እና የተደራሽነት አገልግሎቶችን ለማሻሻል ያለመ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X