ታንዛኒያ በአዲስ ዘመናዊ ተቋም የቀጣናው የካንሰር ህክምና ማዕከል ልትሆን ነው

ሰብስክራይብ

ታንዛኒያ በአዲስ ዘመናዊ ተቋም የቀጣናው የካንሰር ህክምና ማዕከል ልትሆን ነው

​ በዶዶማ በሚገኘው ቤንጃሚን ምካፓ ሆስፒታል ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የካንሰር ስልጠናና ህክምና የልህቀት ማዕከል "ለወደፊቱ ትልቅ እቅድ" እንዳለ የሚያሳይ መሆኑን የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ቀጣናዊ ዳይሬክተር ጋሻው ገበየሁ  ወልዴ ገልጸዋል።

የሆስፒታሉ ተጠባባቂ ስራ አስፈፃሚ ሄንሪ ሁምባ፣ "ተቋሙ ዓለም አቀፍ ደረጃን በሚያሟላ መልኩ የተነደፈ ሲሆን፣ ዘመናዊ የራዲዮቴራፒ እና የኦንኮሎጂ አገልግሎቶችን ይሰጣል" ብለዋል።

ማዕከሉ፣ የመጀመሪያ ታካሚዎቹን በመስከረም ወር መቀበል እንደሚጀምርም አክለዋል።

ጋሻው፣ "ተቋሙ ከጎረቤት ሀገራት የሚመጡ ታካሚዎችን የሚቀበል ማዕከል እንዲሆን ይደረጋል። ዋናው ቁልፍ ጉዳይ ግን በሰው ኃይል ላይ ጠንከር ያለ ኢንቨስትመንት ማድረግ ነው" በማለት አፅንዖት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0