ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለባቸው የፀሐይ ኃይል ገበያዎች አንዷ ሆና ተመደበች
19:56 04.02.2026 (የተሻሻለ: 20:04 04.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለባቸው የፀሐይ ኃይል ገበያዎች አንዷ ሆና ተመደበች
የዓለም አቀፉ የፀሐይ ኃይል ምክር ቤት ባወጣው አዲስ የቅድመ ትንበያ ሪፖርት፤ ኢትዮጵያን እ.ኤ.አ ከ2026-2029 በዘርፉ "ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ" ስምንት የአፍሪካ ሀገራት ተርታ መድቧታል።
በሀገሪቱ በየዓመቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት በ12 በመቶ ማደጉ፤ ሀገሪቱን ለአነስተኛና ትላልቅ የፀሐይ ኃይል ኢንቨስትመንቶች ተመራጭ ያደርጋታል ሲል አመልክቷል።
መንግሥት በ2030 የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን 75 በመቶ ለማድረስ በቀረጸው፤ "ሁለተኛው ምዕራፍ ብሔራዊ የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም" ዕቅድ ውስጥ፤ ለፀሐይ ኃይልና ለባትሪ ማከማቻ ቴክኖሎጂዎች ቅድሚያ መስጠቱ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራት ወደፊት መምጣት፤ አፍሪካ እ.ኤ.አ በ2025 ብቻ ወደ 4.5 ጊጋ ዋት የሚጠጋ አዲስ የፀሐይ ኃይል አቅም እንድትገነባና ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ54 በመቶ ጭማሪ እንድታስመዝግብ አድርጓል ሲል ሪፖርቱ አመልክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X