ኢትዮጵያ የግብርና የምክር አገልግሎትን በሰው ሠራሽ አስተውሎት እና በዲጂታል መታወቂያ ልታዘምን ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የግብርና የምክር አገልግሎትን በሰው ሠራሽ አስተውሎት እና በዲጂታል መታወቂያ ልታዘምን ነው
ኢትዮጵያ የግብርና የምክር አገልግሎትን በሰው ሠራሽ አስተውሎት እና በዲጂታል መታወቂያ ልታዘምን ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.02.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የግብርና የምክር አገልግሎትን በሰው ሠራሽ አስተውሎት እና በዲጂታል መታወቂያ ልታዘምን ነው

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ከ30 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ "OpenAgriNet" የተሰኘ ብሔራዊ የዲጂታል መሠረተ ልማት ይፋ አድርጓል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት በመታገዝ ለአርሶ አደሮች የድምፅ መረጃን፣ በአካባቢ ቋንቋ የሚሰጥ ምክርን እና ለአፈርና አየር ንብረት ሁኔታ የግብርና መፍትሄዎችን ያቀርባል ተብሏል።

ፕሮጀክቱን ለመተግበር ከሕንድ ኩባንያ ጋር የ2.75 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት የተፈረመ ሲሆን በ17 ወራት ውስጥ ተገንብቶ እንደሚጠናቀቅ ተጠቁሟል።

🪪 መድረኩ ከሀገሪቱ የዲጂታል መታወቂያ ጋር በመቀናጀት አርሶ አደሮች የፋይናንስ፣ የገበያ እና የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።

ቴክኖሎጂው በቅርቡ ይፋ ከሆነው የኢትዮጵያ ዲጂታል ግብርና ፍኖተ-ካርታ ጋር የተጣጣመ እና በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ የአርሶ አደሩን ገቢ በአማካይ በ8 በመቶ ያሳድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0