መንግሥት በነዳጅ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ድጎማ ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ እንደሚያነሳ ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱመንግሥት በነዳጅ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ድጎማ ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ እንደሚያነሳ ተገለፀ
መንግሥት በነዳጅ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ድጎማ ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ እንደሚያነሳ ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.02.2026
ሰብስክራይብ

መንግሥት በነዳጅ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ድጎማ ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ እንደሚያነሳ ተገለፀ

መንግሥት ላለፉት አራት ዓመታት ሲያደርግ የነበረውን ድጎማ በቀጣዩ ወር መጨረሻ ሙሉ በሙሉ እንደሚያቆም መረጃው ደርሶኛል ሲል የሀገር ውስጥ የግል ሚዲያ ዘግቧል፡፡

ይህን ተከትሎም የሀገር ውስጥ የነዳጅ ግብይት በዓለም አቀፍ የገበያ ዋጋ መሠረት እንደሚመራ ዘገባው ጨምሮ ገልጿል፡፡

ውሳኔው በኢኮኖሚ ማሻሻያው መሠረት መንግሥት ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር የገባው ውል አካል ነው ተብሏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የድጎማ አሠራሩ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን የነዳጅ ዋጋ ልዩነት በማስፋት በመንግሥት በጀት ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠሩን በትናንቱ የምክር ቤት ቆይታቸው መናገራቸው ይታወሳል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0