በኦሮሚያ ክልል ሁለት የካንሰር ህክምና ማዕከላት እየተገነቡ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ
18:32 04.02.2026 (የተሻሻለ: 18:34 04.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኦሮሚያ ክልል ሁለት የካንሰር ህክምና ማዕከላት እየተገነቡ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ
በባሌ ሮቤ እና በቡራዩ ከተሞች የሚገነቡት የካንሰር ህክምና ማዕከላቱ ግንባታቸው በቀጣይ ሁለት ዓመት ውስጥ ተጠናቆ ወደ ሥራ እንደሚገቡ የክልሉ የጤና ቢሮ ኃላፊ ነጻነት ወርቅነህ ተናግረዋል፡፡
ማዕከላቱ የካንሰር ህክምና የሚጠይቀውን ከፍተኛ ወጪ እና የአገልግሎት ውስንነቱን ታሳቢ በማድረግ ለማኅበረሰቡ ተደራሽ የማድረግ ዓላማን ያነገቡ መሆናቸን ኃላፊዋ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልፀዋል፡፡
በካንሰር የተጠቁ አብዛኞቹ ታማሚዎች ከሀገር ውጪ ተጉዘቅው እንደሚታከሙ እና በክልሉ የጤና ቱሪዝምን ለማስፋፋት እየተሠራ እንደሆነም አንስተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X