የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመምህራን የመኖሪያ ቤት ግንባታን አስጀመረ
18:22 04.02.2026 (የተሻሻለ: 18:24 04.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመምህራን የመኖሪያ ቤት ግንባታን አስጀመረ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበር ለተደራጁ 6 ሺህ 194 የከተማዋ መምህራን የቤት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ጥለዋል።
ቤቶቹ በ57 ማኅበራት ተደራጅተው የቤቱን ዋጋ 25 በመቶ ለቆጠቡ መምህራን እንደሚገነቡ ታውቋል፡፡
ቁልፍ መረጃዎች፦
ከተማ አስተዳደሩ ለግንባታው በወቅታዊ ዋጋ 24 ቢሊዮን ብር ያወጣል፡፡
40 ሄክታር መሬት በነፃ ያቀርባል፡፡
አስተዳደሩ ለቦታው 5 ቢሊዮን ብር የካሳ ግምት ከፍሏል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት እየሠራው ነው ብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X