የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽን የግማሽ ቢሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
17:59 04.02.2026 (የተሻሻለ: 18:04 04.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽን የግማሽ ቢሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
ተቋሙ በቅርቡ የተቋቋመውን ኮሚሽን ለማጠናከር ከገንዘብ በተጨማሪ 67.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ሁለት ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን በድጋፍ እንደሰጠ አስታውቋል።
ድጋፉ ኮሚሽኑ የተቋቋመበትን ሀገራዊ የኢነርጂ ፍላጎት የማሟላት ግብ እንዲያሳካና የጀመራቸውን ሥራዎች እንዲያፋጥን ታስቦ የተደረገ መሆኑን የኤሌክትሪክ ኃይል ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደመረ አሰፋ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽን ሀገሪቱ ለሰላማዊ ዓላማ የሚውል የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት የያዘችውን ዕቅድ በሕግና በቁጥጥር ማዕቀፍ ለመምራት ጥቅምት 2018 ዓ.ም መቋቋሙ ይታወቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X