በኢትዮጵያ የመጥፋት ስጋት ተደቅኖባቸው የነበሩት የ “ቁንድዶ” የዱር ፈረሶች ቁጥር መሻሻሉ ተገለፀ
17:09 04.02.2026 (የተሻሻለ: 17:14 04.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የመጥፋት ስጋት ተደቅኖባቸው የነበሩት የ “ቁንድዶ” የዱር ፈረሶች ቁጥር መሻሻሉ ተገለፀ
በምስራቅ ሐረርጌ በሚገኝ ተራራ ላይ የሚኖሩት የዱር ፈረስ ዝርያዎቹ በአካባቢው በተከናወነ የጥበቃና እንክብካቤ ሥራ ቁጥራቸው አሁን ላይ ከ40 በላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ብዝኃ ሕይወት ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር አብዮት ብርሀኑ “የቁንድዶ ፈረሶች መገኛ በተራራ አናት ላይ ባለ ሜዳ መሆኑና ያለው የቦታ ስፋት ውስን መሆኑ ቁጥራቸው ከዚህ በላይ በፍጥነት እንዳይጨምር አንዱ ምክንያት ቢሆንም፣ አሁን የተመዘገበው ቁጥር ለዝርያው ከመጥፋት መዳን ትልቅ ተስፋ የሰጠ ነው” ማለታቸውን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ከፈረሶቹ በተጨማሪ በሽታን የመቋቋም አቅም ያለውና በተመሳሳይ የመጥፋት ስጋት ውስጥ የነበረው የ“ሼኮዳይ” የዳልጋ ከብት ዝርያ ቁጥርም ከ8 ሺህ በላይ መድረሱን ገልፀዋል፡፡
በዓለም አቀፉ የተፈጥሮ ጥበቃ ሕብረት መመዘኛ መሠረት በአፍሪካ ብቸኛ የዱር ፈረስ ዝርያ እንደሆኑ የሚገመቱት የቁንድዶ ፈረሶች "ለጥፋት አደጋ የተጋለጡ" በሚል ምድብ ውስጥ ተካተው እንደነበረ ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X