https://amh.sputniknews.africa/20260204/3129465.html
ለአፍሪካ ኅብረት እንግዶች የኢትዮጵያን ባሕል ለማስተዋወቅ ተዘጋጅተናል - ደ ሊኦፖል ሆቴል
ለአፍሪካ ኅብረት እንግዶች የኢትዮጵያን ባሕል ለማስተዋወቅ ተዘጋጅተናል - ደ ሊኦፖል ሆቴል
Sputnik አፍሪካ
ለአፍሪካ ኅብረት እንግዶች የኢትዮጵያን ባሕል ለማስተዋወቅ ተዘጋጅተናል - ደ ሊኦፖል ሆቴል የአኅጉሪቱ የዲፕሎማሲ መዲና ከየካቲት 4 እስከ 8 ለሚካሄደው 39ኛው ዓመታዊ የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ዝግጅቷን እያጧጧፈች ነው፡፡ ከዚህ በፊት በተካሄዱት... 04.02.2026, Sputnik አፍሪካ
2026-02-04T16:21+0300
2026-02-04T16:21+0300
2026-02-04T16:34+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/02/04/3129556_0:42:800:492_1920x0_80_0_0_2f607b3918e077d54d7ffcdcb04ab63c.jpg
ለአፍሪካ ኅብረት እንግዶች የኢትዮጵያን ባሕል ለማስተዋወቅ ተዘጋጅተናል - ደ ሊኦፖል ሆቴል የአኅጉሪቱ የዲፕሎማሲ መዲና ከየካቲት 4 እስከ 8 ለሚካሄደው 39ኛው ዓመታዊ የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ዝግጅቷን እያጧጧፈች ነው፡፡ ከዚህ በፊት በተካሄዱት የኅብረቱ ስብሰባዎች ጥሩ ልምድ ያካበተው ደ ሊኦፖል ዓለም አቀፍ ባለ አራት ኮከብ ሆቴል ለጉባኤው የሚመጡ እንግዶቹን ለመቀበል መዘጋጀቱን ገልጿል፡፡ "ከዚህ በፊት በነበረው የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ወቅት ጥሩ ልምድ ነበረን። አገልግሎታችንን ተጠቅመው፣ ባሕላችንን አይተው ይሄዳሉ። በቀጣይም የነበረውን እርካታ ጠብቀን ለመቀጠል ነው የምናቅደው” ሲሉ የደ ሊኦፖል ሆቴል የሽያጭ እና ማርኬቲንግ ማናጀር ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።ሆቴሉ ከአኅጉሪቱ የተለያዩ ሀገራት ለሚመጡ እንግዶቹ የምግብ ዝግጅት እያደርገ እንዲሁም ከፖሊስ ጋር በመተባበር የጸጥታ ጉዳዮችን ከወዲሁ ዳር ዳር እያሲያዘ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ “ባሕላዊ ለምሳሌ 'ኡጋሊ' እና መሰል ምግቦችን ጨምሮ በሬስቶራንታችን እና በቁርስ አገልግሎታችን ላይ አካትተናል። ሌላው ደህንነት ላይ ነው። ከአካባቢው ፖሊስ ጋር በመተባበር የተለያዩ ስብሰባዎችን እና ሥልጠናዎችን አድርገናል። የራሳችንም ጥበቃ አለን፣ ከመንግሥትም የሚመደብልን ጥበቃ ይኖራል። ሌላው ባሕላችንን ማስተዋወቅ ላይ ነው። ከስታፎቻችን አቀባበል ጀምሮ የቡና ሥነ-ሥርዓት፣ አለባበስ እና የፀጉር አሠራርን ጨምሮ ኢትዮጵያዊ ባሕልን ለማሳየት ተዘጋጅተናል።” ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2026
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/02/04/3129556_45:0:756:533_1920x0_80_0_0_7d947bc2704931809aaff37be1eba1ae.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
ለአፍሪካ ኅብረት እንግዶች የኢትዮጵያን ባሕል ለማስተዋወቅ ተዘጋጅተናል - ደ ሊኦፖል ሆቴል
16:21 04.02.2026 (የተሻሻለ: 16:34 04.02.2026) ለአፍሪካ ኅብረት እንግዶች የኢትዮጵያን ባሕል ለማስተዋወቅ ተዘጋጅተናል - ደ ሊኦፖል ሆቴል
የአኅጉሪቱ የዲፕሎማሲ መዲና ከየካቲት 4 እስከ 8 ለሚካሄደው 39ኛው ዓመታዊ የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ዝግጅቷን እያጧጧፈች ነው፡፡ ከዚህ በፊት በተካሄዱት የኅብረቱ ስብሰባዎች ጥሩ ልምድ ያካበተው ደ ሊኦፖል ዓለም አቀፍ ባለ አራት ኮከብ ሆቴል ለጉባኤው የሚመጡ እንግዶቹን ለመቀበል መዘጋጀቱን ገልጿል፡፡
"ከዚህ በፊት በነበረው የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ወቅት ጥሩ ልምድ ነበረን። አገልግሎታችንን ተጠቅመው፣ ባሕላችንን አይተው ይሄዳሉ። በቀጣይም የነበረውን እርካታ ጠብቀን ለመቀጠል ነው የምናቅደው” ሲሉ የደ ሊኦፖል ሆቴል የሽያጭ እና ማርኬቲንግ ማናጀር ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
ሆቴሉ ከአኅጉሪቱ የተለያዩ ሀገራት ለሚመጡ እንግዶቹ የምግብ ዝግጅት እያደርገ እንዲሁም ከፖሊስ ጋር በመተባበር የጸጥታ ጉዳዮችን ከወዲሁ ዳር ዳር እያሲያዘ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡
“ባሕላዊ ለምሳሌ 'ኡጋሊ' እና መሰል ምግቦችን ጨምሮ በሬስቶራንታችን እና በቁርስ አገልግሎታችን ላይ አካትተናል። ሌላው ደህንነት ላይ ነው። ከአካባቢው ፖሊስ ጋር በመተባበር የተለያዩ ስብሰባዎችን እና ሥልጠናዎችን አድርገናል። የራሳችንም ጥበቃ አለን፣ ከመንግሥትም የሚመደብልን ጥበቃ ይኖራል። ሌላው ባሕላችንን ማስተዋወቅ ላይ ነው። ከስታፎቻችን አቀባበል ጀምሮ የቡና ሥነ-ሥርዓት፣ አለባበስ እና የፀጉር አሠራርን ጨምሮ ኢትዮጵያዊ ባሕልን ለማሳየት ተዘጋጅተናል።”
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X