አፍሪካ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ የወርቅ ክምችቷን መቆጣጠር አለባት - ደቡብ አፍሪካዊ ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ የወርቅ ክምችቷን መቆጣጠር አለባት - ደቡብ አፍሪካዊ ባለሙያ
አፍሪካ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ የወርቅ ክምችቷን መቆጣጠር አለባት - ደቡብ አፍሪካዊ ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.02.2026
ሰብስክራይብ

አፍሪካ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ የወርቅ ክምችቷን መቆጣጠር አለባት - ደቡብ አፍሪካዊ ባለሙያ

የወርቅ ክምችታቸውን ማግኘት የማይችሉ ሀገራት በቀላሉ በከፊል ሉዓላዊነታቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ ሲሉ በደቡብ አፍሪካ ኔልሰን ማንዴላ ዩኒቨርሲቲ የልማት ፋይናንስ ዶክትሬት ያላቸው ታፋድዝዋ ሩዚቭ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሀገራት ክምችታቸውን ማስተዳደር ወይም ማስፋት በሚፈልጉበት ወቅት በኒውዮርክ፣ ለንደን ወይም ዱባይ በተቀመጠ ወርቅ ላይ መተማመን እንደማይቻል አስጠንቅቀዋል።

አፍሪካ በአኅጉሪቱ ውስጥ ቁጥጥር የሚደረግበት የወርቅ ማዕከል ቢኖራት ተጠቃሚ ልትሆን ትችላለች። በጋና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዚምባብዌ እና በሳኅል ሀገራት ውስጥ የተትረፈረፈ ክምችት መኖሩን የጠቀሱት ሩዚቭ፤ ወርቁ በአኅጉሪቱ እንዲቆይና ከልማት ግቦች ጋር ለማጣጣም የአፍሪካ፣ የሩሲያ እና የቻይና ባለሙያዎችን ጥምረት በመጠቀም ስኬታማ ለመሆን ምንም ዓይነት የቴክኒክ መሰናክል እንደማይታያቸው ገልጸዋል።

የሁኔታ ትንበያቸውን ሲያስቀምጡም፤ የአፍሪካ የወርቅ ክምችት በወርቅ ለሚደገፍ የመጠባበቂያ ገንዘብ መሠረት በመሆን የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና እና የፓን አፍሪካ የክፍያ ሥርዓትን የመሳሰሉ ተነሳሽነቶችን ሊደግፍ ይችላል ብለዋል። ሆኖም ሩዚቭ “የአውሮፓ ኅብረት ወጥመድ” እንዳይደገም አስጠንቅቀዋል።

ይህ የሚሆን ከሆነ፤ በደቡብዊው ዓለም እና በብሪክስ ሀገራት መካከል ያለውን ንግድ ሊያሳድጉ የሚችሉ ከስዊፍት ውጭ ያሉ አማራጮችን መፍጠር ጨምሮ፤ የፋይናንስ ነፃነት ለማምጣት ትልቅ እርምጃ አድርገው እንደሚመለከቱት አጽንኦት ሰጥተዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0