መንግሥት የውጭ ድጋፍ መቆራረጥ በጤና ዘርፉ ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቋቋም 14 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ በጀት መመደቡ ተሰማ
17:27 03.02.2026 (የተሻሻለ: 17:34 03.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
መንግሥት የውጭ ድጋፍ መቆራረጥ በጤና ዘርፉ ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቋቋም 14 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ በጀት መመደቡ ተሰማ
ገንዘቡ ለቤተሰብ እቅድና ለሥነ-ተዋልዶ ጤና ግብዓቶች ግዥ የሚውል መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥነ-ሕዝብ ፈንድ ከዚህ ቀደም የእነዚህን ግብዓቶች ግዢ ይደግፍ ነበር ተብሏል፡፡
ሚኒስቴሩ በዘረጋው "ኮምፓክት አግሪመንት" የተባለ አዲስ የአሠራር ስርዓት፤ መንግሥትና አጋር ድርጅቶች በጋራ በሚያደርጉት የገንዘብ መዋጮ የምዕራባውያን ሀገራት የፖሊሲ ለውጦች የሚፈጥሩትን ስጋት በዘላቂነት ለመፍታት እንደታሰበ ተገልጿል።
እርምጃው አሁን ላይ በተለይም በትራምፕ አስተዳደር ተለዋዋጭ ፖሊሲ ምክንያት በዓለም አቀፍ ድጋፍ ዙሪያ አለመረጋጋት መፈጠሩን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X