በሶማሊያ ለሚሠማሩ የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ኃይሎች ሥልጠና መስጠት እንደጀመረ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ
16:29 03.02.2026 (የተሻሻለ: 17:34 03.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሶማሊያ ለሚሠማሩ የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ኃይሎች ሥልጠና መስጠት እንደጀመረ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ
🪖 በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍና የማረጋጋት ተልዕኮ (አውሶም) ስር የሚሠማሩት የሰላም ማስከበር ኃይሎች በሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ሥልጠና እየተሠጣቸው እንደሚገኝ ተገልጿል።
ሠልጣኞች ወታደራዊ ቴክኒካዊ ክህሎቶች፣ ጀነሪክ ስልጠናዎች፣ ተልዕኮ-ተኮር እና ልዩ ሙያዊ ሥልጠናዎችን እንደሚሰጣቸው የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ምክትል አዛዥና የሥልጠና ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ገነነው ቶላ ተናግረዋል።
ሥልጠናው ለ90 ቀናት እንደሚቆይ የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

