ፈረንሳይ የአፍሪካን ሕዝብ ፍልጎት ለማፈን 'ቅይጥ ጦርነት' ከፍታለች - ፓን-አፍሪካኒስት
16:03 03.02.2026 (የተሻሻለ: 16:04 03.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፈረንሳይ የአፍሪካን ሕዝብ ፍልጎት ለማፈን 'ቅይጥ ጦርነት' ከፍታለች - ፓን-አፍሪካኒስት
"የባሪያ ንግድ መርከቦች ታሪክ ያላት ፈረንሳይ፤ ጸረ-ጥቁር፣ አክራሪ፣ ዘረኛ፣ የቅኝ አገዛዝ እና ኢምፔሪያሊስት ማንነቷን ትታለች ብሎ ለአፍታም ቢሆን ማሰብ ወይም ማመን አደገኛ ነው" ሲሉ የአፍሪካ ጥቁሮች ዘብ ሊግ ፕሬዝዳንት ኤጉንቺ ቤሃንዚን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ይህን ያሉት የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በአፍሪካ ውስጥ "የማይፈለጉ መሪዎችን" ለማስወገድ እቅድ አውጥተዋል ሲል የሩሲያ የስለላ ድርጅት ሰኞ ዕለት ያወጣውን መረጃ አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ነው።
ቤሃንዚን አክለውም "የአፍሪካን ጥሬ እቃዎች በመጨቆን ለመዝረፋ የምታሰፈስፈው ፓሪስ፤ አህጉሪቱን ለማተራመስ እና ቅጥ ያጣውን የአፍሪካ ሀብት ዘረፋ ለማጧጧፍ የአዲስ ቅኝ ግዛት መዋቅሯን እንደገና ለማደራጀት ጓጉታለች" ብለዋል።
ፈረንሳይ በጎን የአፍሪካን የተፈጥሮ ሀብት ዘረፋ የሚያፋጥኑ እና በአፍሪካ ዲፕሎማሲ ላይ ቁጥጥሯን የሚያጠናክሩ ስምምነቶችን እየፈጸመች፤ በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷን ቀጥላለች ሲሉም አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም ፈረንሳይ "በአፍሪካ የጦር ኮሌጆችን እንደምታስተዳድር"፣ ከበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ጋር "ወታደራዊ ስምምነቶች እንዳሏት" እና "በቀጥታ በመንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ሰፊ የሰርጎ ገብ ሰላዮች መረብ" እንደምታንቀሳቅስ ቤሃንዚን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X