የኔቶ ጦር የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ወዲያውኑ ወደ ዩክሬን ይገባል - የኔቶ ዋና ጸሐፊ
15:19 03.02.2026 (የተሻሻለ: 15:24 03.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኔቶ ጦር የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ወዲያውኑ ወደ ዩክሬን ይገባል - የኔቶ ዋና ጸሐፊ
ማርክ ሩተ ለዩክሬን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር፤ ለዩክሬናውያን የሚቻለውን ወታደራዊ ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉ እና የኔቶ ደህንነት በቀጥታ በዩክሬን ጥረት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ገልጸዋል።
ሩተ የሰጧቸው ተጨማሪ መግለጫዎች፦
የኔቶ ሀገራት ለዩክሬን ፈጣን ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ ናቸው፡፡
ጥምረቱ ካለፈው በጋ ጀምሮ 90 በመቶ የሚሆኑ የአየር መከላከያ መሳሪያዎችን እንዲሁም ዩክሬን ከጠየቀቻቸው ሚሳኤሎች ውስጥ 75 በመቶውን ለኪዬቭ አቅርቧል፡፡
የጦር ኃይላቸውን ወደ ዩክሬን ለመላክ ያልተስማሙ የኔቶ አባላት በሌሎች መንገዶች ድጋፍ ያደርጋሉ ያሉት ሩተ፤ እንዴት ለሚለው ግን ዝርዝሩን አልጠቀሱም፡፡
ኔቶ ፈጠራን በልዩ ሁኔታ ተግባራዊ እያደረገች ካለችው ዩክሬን ትምህርት እየቀሰመ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ፤ ሩሲያ የአውሮፓ ኅብረት ጦር በዩክሬን መሰማራትን እንደ ጣልቃ ገብነት እንደምትቆጥረው ቀደም ብለው በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X