የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቋርጦት የነበረውን የመቀሌ በረራ ዳግም አስጀምረ

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቋርጦት የነበረውን የመቀሌ በረራ ዳግም አስጀምረ

አየር መንገዱ ከጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 5 ቀናት ወደ ትግራይ ክልል የሚደረገውን በረራ አቋርጦ የቆየ ቢሆንም ዛሬ ማክሰኞ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ዳግም በረራ መጀመሩን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

በበረራው መቋረጥ ሳቢያ ከሰሞኑን እረፍት ላይ የነበሩ የመቀሌ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ሠራተኞች ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል፡፡

ℹ እንደ ፍላይት ራዳር 24 የበረራ መቆጣጠሪያ ድረ ገፅ መሠረት፤ የበረራ ቁጥር ኢቲ102 የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ከቦሌ አየር ማረፊያ ተነስቶ ወደ መቀሌ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ አቅንቷል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0