ፈረንሳይ ተፅዕኖዋን ካጣችበት ግዜ ጀምሮ አፍሪካን ለማተራመስ እየሞከረች ነው - ማሊያዊ ተንታኝ
20:01 02.02.2026 (የተሻሻለ: 20:04 02.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፈረንሳይ ተፅዕኖዋን ካጣችበት ግዜ ጀምሮ አፍሪካን ለማተራመስ እየሞከረች ነው - ማሊያዊ ተንታኝ
"የፈረንሳይን ጦር ከባረርን በኋላ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሀገሮቻችንን ለማተራመስ የሚደረጉ ሙከራዎች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል" ሲሉ ማሊያዊው ጦማሪ ኢቡ ሲ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ይህን ያሉት የሩሲያ የደህንነት ተቋም ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ ማክሮን በአፍሪካ "የማይፈለጉ መሪዎችን" ለማስወገድ እንዳቀዱ መገለጹን በተመለከተ አስተያየታቸውን በሰጡበት ወቅት ነው።
በማሊ የነዳጅ ጫኝ መኪናዎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ጠቅሰዋል፡፡ ለዚህም ባማኮ "ከሩሲያ አጋሮች ጋር መፍትሔ እያገኘችለት ነው" ብለዋል። በተጨማሪም በጥር ወር በቡርኪና ፋሶ የተሞከረውን መፈንቅለ መንግሥት እና በኒያሜ አየር ማረፊያ ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት እንደ ምሳሌ አንስተዋል።
"አለመታደል ሆኖ ከእነዚህ ድርጊቶች በስተጀርባ ሁልጊዜም የፈረንሳይ መሪዎች እንዳሉ እናውቃለን" ብለዋል። አክለውም የፈረንሳይ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም "አውሮፓን ለማዳን ፈረንሳይ ወደ አፍሪካ መመለስ አለባት" በማለት በግልጽ መናገራቸውን አስታውሰዋል።
ኢላማ የተደረጉት የሳኅል ሀገራት ጥምረት ሀገራት ብቻ አይደሉም። ማዳጋስካርም በፓሪስ እይታ ውስጥ ትገኛለች ያሉት ኢቡ ሲ፤ ሞስኮ በጉዳዩ ላይ የሰጠችውን ማስጠንቀቂያ በመጥቀስ ፈረንሳይ "አዲሱን [የማዳጋስካር] ፕሬዚዳንት ለመጣል" እንደምትፈልግ አመልክተዋል።
"ሕዝባችን ይህንን ሊገነዘብ ይገባል፤ በአሁኑ ወቅት በማክሮን አገዛዝ እየተካሄደ ያለውን ያልተለመደ ጥቃት አውቀው በፅናት መቆማቸው ወሳኝ ነው" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X