"ፈረንሳይ አሁንም በሀገሮቻችን ውስጥ ከሚከሰቱ የሽብር ድርጊቶች ጀርባ አለች" - ማሊያዊ ተንታኝ
18:17 02.02.2026 (የተሻሻለ: 18:24 02.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"ፈረንሳይ አሁንም በሀገሮቻችን ውስጥ ከሚከሰቱ የሽብር ድርጊቶች ጀርባ አለች" - ማሊያዊ ተንታኝ
“ኢማኑኤል ማክሮን በእርግጥም የሳኅል ጥምረት አባል ሀገራት ለምዕራባውያን ፍላጎት ላለመገዛት በመወሰናቸው ምክንያት የበቀል እርምጃ መውሰድ ይፈልጋሉ” ሲሉ አብዱላዬ ዲያሎ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
እንደ የማሊ ተሀድሶ ስብስብ የኮሙኒኬሽን ኦፊሰር ገለፃ፤ ፈረንሳይ “የአላዋቂነት ዘመን ማብቃቱን ዘንግታለች።”
“ቀደም ሲል አፍሪካን ለምሬት ከዳረጉ ልሂቃን ጋር በመመሳጠር ፈረንሳይ ሀብቶችን ስትዘርፍና ስትሰርቅ ቆይታለች። ዛሬ ግን ሁኔታው ፍጹም ተቃራኒ ነው” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።
ተንታኙ አክለውም የወቅቱ የሳኅል ሀገራት ጥምረት መሪዎች “በሕዝቦቻቸው የሚደገፉ” መሆናቸውንና በጂኦፖለቲካዊ እና በሀብት ረገድ “የግጭት ማዕከል” በሆነው የሳኅል ቀጣና ዙሪያ “ከሩሲያ ጋር መረጃ እንደሚለዋወጡ” ገልጸዋል።
ፈረንሳይ በአፍሪካ አሁንም የአኅጉሪቱን የተፈጥሮ እና የማዕድን ሀብቶች መቆጣጠር ነው የምትፈልገው ሲሉ ዲያሎ ጠቁመዋል።
“ፈረንሳይ የፈለገችውን እስካላገኘች ድረስ ጥቅሟን የሚያደናቅፉ የሀገር መሪዎችን ለማስወገድ ሁልጊዜም የግል ጥቅም ላይ ያተኮሩ የሽብር መንገዶችን ለመተግበር ትሞክራለች።”
የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት ፓሪስ በተለይም በሳኅል ቀጣና መፈንቅለ መንግሥቶችን እያዘጋጀችና አሸባሪዎችን እየደገፈች መሆኑን ቀደም ሲል መግለጹ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X