ናይጄሪያዊው ሙዚቀኛ ፌላ ኩቲ የግራሚ የሕይወት ዘመን ስኬት ሽልማት ተበረከተለት
16:46 02.02.2026 (የተሻሻለ: 16:54 02.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ናይጄሪያዊው ሙዚቀኛ ፌላ ኩቲ የግራሚ የሕይወት ዘመን ስኬት ሽልማት ተበረከተለት
ፌላ ኩቲ ከሙዚቀኛም በላይ ነበር ያሉት የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኒቡ፤ "ፌላ ደፋር የሕዝብ ድምፅ፣ የነፃነት ፈላስፋ እንዲሁም በሙዚቃው ኢ-ፍትሐዊነትን የታገለና የዓለምን የሙዚቃ ቅኝት የቀየረ አብዮታዊ ኃይል ነበር" ሲሉ ከሞት በኋላ ያገኘውን የግራሚ ሽልማት ተከትሎ ክብራቸውን በገለጹበት መግለጫ ተናግረዋል፡፡
◻ ፌላ፤ በሎስ አንጀለስ በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት የግራሚ የሕይወት ዘመን ስኬት ሽልማትን ከሞት በኋላ የተቀበለ የመጀመሪያው አፍሪካዊ አርቲስት ሆኗል።
◻ ሽልማቱ ለፌላ ዓለም አቀፋዊና ዘላለማዊ ተጽዕኖ እንዲሁም ዘመናዊውን የአፍሪካ ሙዚቃ በመቅረጽ ረገድ ለተጫወተው ሚና እውቅና ሰጥቷል።
◻ የሟቹ አርቲስት ልጆች፤ ሙዚቀኛው ፌሚ ኩቲን ጨምሮ ከናይጄሪያው የአፍሮቢት ኮከብ ዴቪዶ ጋር በመሆን ሽልማቱን ተቀብለዋል።
ፌላ ኩቲ በ1970ዎቹ የጃዝ፣ የፈንክ እና የአፍሪካ ምቶች ውህደት የሆነውን አፍሮቢት በመፍጥር በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚታወቀው የአፍሮቢትስ የሙዚቃ ዘውግ መንገድ ጠርጓል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X