የሳኅል ሀገራት ጥምረት ኃይሎች በደርዘን የሚቆጠሩ ታጣቂዎችን ደመሰሱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሳኅል ሀገራት ጥምረት ኃይሎች በደርዘን የሚቆጠሩ ታጣቂዎችን ደመሰሱ
የሳኅል ሀገራት ጥምረት ኃይሎች በደርዘን የሚቆጠሩ ታጣቂዎችን ደመሰሱ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.02.2026
ሰብስክራይብ

የሳኅል ሀገራት ጥምረት ኃይሎች በደርዘን የሚቆጠሩ ታጣቂዎችን ደመሰሱ

የሳኅል ሀገራት ጥምረት የጋራ ኃይሎች በታላቁ ሰሃራ የእስልምና መንግሥት ቡድን (አይኤስጂኤስ)* ላይ በፈጸሙት የአየር ድብደባ፤ ሞተር ሳይክሎችንና ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ የቡድኑን የሎጂስቲክ ንብረቶች እንዳወደሙ የጥምረቱ መግለጫ አመልክቷል።

የማሊ ጦር ኃይሎች በበኩላቸው አቡ አልጋባስ ኢችማሊ የተባለውንና በአካባቢው በንጹሐን ዜጎች ላይ ለሚፈጸሙ የከፉ በደሎች ተጠያቂ የሆነውን ከፍተኛ የቡድኑን አመራር መግደላቸውን አስታውቀዋል።

ጥቃቱ የተፈጸመው ከኒጀር ድንበር አቅራቢያ፣ ከሜናካ ከተማ ደቡባዊ ክፍል፣ አካባር በተባለ አካባቢ ነው።

*በሩሲያ እና በሌሎች በርካታ ሀገራት በአሸባሪነት የተፈረጀ ቡድን

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0