ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በኮትዲቯር የኮኮዋ ምርት ዋጋ ላይ ያላቸውን ቁጥጥር ለመመከት የመፍትሄ ሃሳብ አቀረቡ
16:16 02.02.2026 (የተሻሻለ: 16:24 02.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በኮትዲቯር የኮኮዋ ምርት ዋጋ ላይ ያላቸውን ቁጥጥር ለመመከት የመፍትሄ ሃሳብ አቀረቡ
ኮትዲቯር የዓለምን 40 በመቶ የኮኮዋ ፍላጎት ብትሸፍንም እንደሌሎች የአፍሪካ አምራቾች ሁሉ በዋጋው ላይ ያላት ቁጥጥር አነስተኛ እና ለተለዋዋጭ የዓለም ገበያ የተጋለጠ ነው።
የኮትዲቯር የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት ፕሪንስ ቤጋንሱ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት አስተያየት፤ ዋናው መፍትሄ ምርቱ ወደ ውጭ ከመላኩ በፊት በሀገር ውስጥ የሚቀነባበርበትን መሠረተ ልማት ማልማት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ይህ ካልሆነ ግን ሀገሪቱ "ዋጋቸውን በላያችን ላይ ለሚጭኑ ዓለም አቀፍ ተቋማት ትዕዛዝ" ተገዢ ሆና ትቀጥላለች ብለዋል።
በሌላ በኩል የምጣኔ ሀብት ተንታኙ ዣን ሉዊ ባግቦ፤ በአምራቾች መካከል ያለው ትብብር ወሳኝ እንደሆነ ገልጸዋል። ለዚህም የኮትዲቯር እና የጋናን የኮኮዋ ጥምረት ለአምራቾች አንድነት በማሳያነት ጠቅሰዋል።
ጥምረቱ "ላኪዎች ወይም ግዙፍ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ተመጣጣኝ የዋጋ ልዩነት እንዲያደርጉ ተጽዕኖ ማሳደር" አስችሏል ሲሉ ተንታኙ አብራርተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X