በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሰው አልባ ዘመናዊ የፖሊስ ጣቢያ በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
15:10 02.02.2026 (የተሻሻለ: 15:24 02.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሰው አልባ ዘመናዊ የፖሊስ ጣቢያ በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
ይህ አገልግሎት በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ እንደተጀመረ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የቴክኖሎጂ ማስፋፊያ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ደምስ ይልማ ነግረውኛል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ሰው አልባ ጣቢያው፤ ተገልጋዮች በዲጂታል መንገድ በዋናው ማዕከል ከሚገኙ የፖሊስ ኦፊሰሮች ጋር በቪዲዮ እና በድምጽ በመገናኘት ጉዳያቸውን የሚያስፈጽሙበት ነው ተብሏል።
ስለአገልግሎቱ ቁልፍ መረጃዎች፦
◻ ወንጀል የተፈጸመበት ግለሰብ በጂፒኤስና ካሜራ የታገዘ መረጃ ለፓትሮል ፖሊስ በማስተላለፍ ወንጀለኞችን በፍጥነት ለመያዝ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፣
◻ በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ ሱማሊኛ፣ እንግሊዝኛ እና በሌሎች ቋንቋዎችም ይሰጣል፣
◻ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ መተግበሪያ ጋር ተቀናጅቷል፣
◻ የተለያዩ ክፍያዎችን ጨምሮ 46 የሚደርሱ የመንግሥት አገልግሎቶችን መስጠት ይችላል፡፡
የሙከራ አገልግሎቱ ቦሌ ድልድይ አካባቢ እንደተጀመረ የተገለጸ ሲሆን ውጤታማነቱ ታይቶ ወንጀልና የሕዝብ እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው እንደ መርካቶ እና መገናኛ ባሉ አካባቢዎች እንደሚስፋፋ ተገልጿል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X