ናይጄሪያ የቤኒንን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ለመመከት የላከችውን ጦር አስወጣች
14:57 02.02.2026 (የተሻሻለ: 17:24 02.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ የቤኒንን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ለመመከት የላከችውን ጦር አስወጣች
የናይጄሪያ ጦር አባላት መረጋጋትን በመመለስ ረገድ ላሳዩት "ሙያዊ ብቃት እና አጋርነት" አድናቆቱን ባወጣው መግለጫ የገለጸው የቤኒን መንግሥት፤ የሁለቱ ሀገራት የጋራ ኦፕሬሽን ለቀጣናዊ ትብብር እንደ አርአያ የሚወሰድ ነው ብሏል።
የቤኒን ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ፍሩክቱ ባጊዲ፤ በሁለቱ ሀገራት ኃይሎች መካከል የነበረውን ውጤታማ ቅንጅት በማድነቅ፤ የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኢኮዋስ) በክልሉ ሰላምን በማስከበር ረገድ ቁልፍ ሚና እንዳለው በድጋሚ አረጋግጠዋል።
ታህሳስ 2025 የተሞከረውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ፤ የሀገሪቱን ተቋማት ለመጠበቅና ሰላምን ለማስፈን በፕሬዚዳንት ፓትሪስ ታሎን ጥያቄ መሠረት በኢኮዋስ በኩል ተሠማርቶ ለነበረውና ወደ 200 የሚጠጉ አባላት ላሉት የናይጄሪያ ሜካናይዝድ እግረኛ ሻለቃ ጦር ይፋዊ የአሸኛኘት ዝግጅት ተደርጎለታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X




