አልጄሪያ ከነፃነት በኋላ ካከናወነቻቸው ‘ታላላቅ ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክቶች’ አንዱን ማጠናቀቋን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አስታወቁ

ሰብስክራይብ

አልጄሪያ ከነፃነት በኋላ ካከናወነቻቸው ‘ታላላቅ ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክቶች’ አንዱን ማጠናቀቋን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አስታወቁ

ፕሬዚዳንት አብደልመጂድ ታቡን በ20 ወራት ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀውን የምዕራብ በሻር–ቲንዱፍ–ጋራ ጀቢሌት የማዕድን ባቡር መስመር በይፋ መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ የተመዘገበው ውጤት የሀገሪቱን ቁርጠኝነት፣ የሀገር ውስጥ የፋይናንስ አቅምን እና ከቻይናውያን አጋሮች የቴክኒክ ድጋፍ ያገኙትን የአልጄሪያ ሙያተኞችን ብቃት የሚያሳይ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።

950 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የባቡር መስመር 2 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ርቀት በመሸፈን በቤቲዋ (ኦራን) ለሚገኘው የቶስያሊ ግሩፕ ፋብሪካ የብረት ማዕድን ግብዓት ያጓጉዛል።

የፕሮጀክቱ ግንባታ በሐምሌ ወር 2014 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን ግዙፉ የማቀነባበሪያ ፋብሪካ ደግሞ በታህሳስ 2016 ዓ.ም ሥራውን ጀምሯል።

ወደ 3.5 ቢሊዮን ቶን የሚጠጋ የብረት ክምችት ያለው የጋራ ጄቢሌት ማዕድን ማውጫ በዓለም ካሉ ግዙፍ የብረት ማዕድን ስፍራዎች አንዱ ነው።

የማዕድን ልማቱ የአልጄሪያን ኢኮኖሚ ከነዳጅና ጋዝ ጥገኝነት በማላቀቅ ለማስፋትና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ባለሥልጣናት ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0