የናይጄሪያ ጦር በሌሊት በፈጸመው ጥቃት ከፍተኛ የቦኮ ሃራም አዛዥን እንዳስወገደ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየናይጄሪያ ጦር በሌሊት በፈጸመው ጥቃት ከፍተኛ የቦኮ ሃራም አዛዥን እንዳስወገደ አስታወቀ
የናይጄሪያ ጦር በሌሊት በፈጸመው ጥቃት ከፍተኛ የቦኮ ሃራም አዛዥን እንዳስወገደ አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.02.2026
ሰብስክራይብ

የናይጄሪያ ጦር በሌሊት በፈጸመው ጥቃት ከፍተኛ የቦኮ ሃራም አዛዥን እንዳስወገደ አስታወቀ

​ በቦርኖ ግዛት በተካሄደ ኦፕሬሽን በሳምቢሳ ደን የቦኮ ሃራም* ምክትል አዛዥ እንደሆነ የተለየው አቡ ካሊድ ከሌሎች 10 አሸባሪዎች ጋር መገደሉን የሀገሪቱ ጦር በመግለጫው አስታውቋል።

​"ሀዲን ካይ" በተሰኘው ኦፕሬሽን እና ከሲቪል ታጣቂዎች ጋር በመተባበር በተፈጸመው በዚህ ጥቃት፤ የጦር መሣሪያዎች፣ ጥይቶች፣ ሞተር ብስክሌቶች፣ የምግብ እና የህክምና ቁሳቁሶች መማረካቸውን የገለጸው መግለጫው፤ በሠራዊቱ በኩል የደረሰ ምንም ዓይነት የህይወት መጥፋት አለመኖሩን አጽንኦት ሰጥቷል።

​ ይህ ድል የተመዘገበው ከፍተኛ የቦኮ ሃራም/የምዕራብ አፍሪካ ክንፍ ኢስዋፕ* አዛዥ በተገደለ በ24 ሰዓታት ውስጥ መሆኑን የጠቀሰው ጦሩ፤ በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ቁልፍ የአሸባሪ መደበቂያዎች ላይ የማጽዳት ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን አክሎ ገልጿል።

* በሩሲያ እና በሌሎች በርካታ ሀገራት የታገዱ አሸባሪ ድርጅቶች

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የናይጄሪያ ጦር በሌሊት በፈጸመው ጥቃት ከፍተኛ የቦኮ ሃራም አዛዥን እንዳስወገደ አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የናይጄሪያ ጦር በሌሊት በፈጸመው ጥቃት ከፍተኛ የቦኮ ሃራም አዛዥን እንዳስወገደ አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0