የካርቱም አውሮፕላን ማረፊያ የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ሁለተኛውን የንግድ በረራ አስተናገደ
18:55 01.02.2026 (የተሻሻለ: 19:14 01.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የካርቱም አውሮፕላን ማረፊያ የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ሁለተኛውን የንግድ በረራ አስተናገደ
የሀገሪቱ መንግሥት የዜና ወኪል እንደዘገበው፤ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያው ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ የመጀመሪያውን የሱዳን አየር መንገድ በረራ በዛሬው ዕለት በፖርት ሱዳን ተቀብሏል።
ይህም ብሔራዊ አየር መንገዱ ግጭቱ ከጀመረ ወዲህ ወደ ዋና ከተማዋ ያደረገው የመጀመሪያ በረራ ሆኖ ተመዝግቧል። የሱዳን አየር መንገድ በህንድ ሀገር ለስድስት ወራት ያህል የቆየ ከፍተኛ የጥገና ሥራ ካከናወነ በኋላ በቅርቡ በረራ ጀምሯል።
በረራው የሱዳን አየር መንገድ የአየር ትራንስፖርትን የመደገፍ፣ ትስስርን የማጠናከር እና ዜጎችን የማገናኘት ብሔራዊ ሚናው ጋር እንደሚጣጣም እንዲሁም በግጭቱ ምክንያት ሕዝቡ የገጠመውን የጉዞ እንግልት ለማቃለል እንደሚረዳ የዜና ወኪሉ ገልጿል።
ይህ አዲስ ምዕራፍ ወደ ካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚደረጉ መደበኛ በረራዎችን ለመጀመር ትልቅ እርምጃ እና የዋና ከተማዋን ማገገም፣ መረጋጋት እና ቀስ በቀስ ወደ መደበኛ ሕይወት መመለስ የሚያመለክት እንደሆነ ሪፖርቱ ጠቁሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia