ናይጄሪያ በ2026 ለዓለም አቀፍ ዕድገት አስተዋጽኦ በማድረግ ቀዳሚዋ የአፍሪካ ሀገር ትሆናለች ሲል ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱናይጄሪያ በ2026 ለዓለም አቀፍ ዕድገት አስተዋጽኦ በማድረግ ቀዳሚዋ የአፍሪካ ሀገር ትሆናለች ሲል ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አስታወቀ
ናይጄሪያ በ2026 ለዓለም አቀፍ ዕድገት አስተዋጽኦ በማድረግ ቀዳሚዋ የአፍሪካ ሀገር ትሆናለች ሲል ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.02.2026
ሰብስክራይብ

ናይጄሪያ በ2026 ለዓለም አቀፍ ዕድገት አስተዋጽኦ በማድረግ ቀዳሚዋ የአፍሪካ ሀገር ትሆናለች ሲል ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አስታወቀ

አይኤምኤፍ ባወጣው ሪፖርት መሠረት፤ ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር እ.ኤ.አ 2026 የ4.4 በመቶ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርት ዕድገት በማስመዝገብ ደቡብ አፍሪካን ቀድማ ለዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ የምታደርግ ቀዳሚዋ የአፍሪካ ሀገር ትሆናለች።

ናይጄሪያ በዚህ ዓመት ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት ዕድገት ውስጥ የ1.5 በመቶ ድርሻ ይኖራታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ይህም በዓለም ከአስሩ ቀዳሚ አስተዋጽኦ አድራጊ ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ እና በዝርዝሩ ውስጥ የምትገኝ ብቸኛዋ አፍሪካዊ ሀገር እንድትሆን ያደርጋታል።

ዕድገቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ማስተካከያ እና የነዳጅ ድጎማ ማንሳትን ጨምሮ የናይጄሪያ መንግሥት በተገበራቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ምክንያት እንደሚመዘግብ አይኤምኤፍ ገልጿል፡፡

ደቡብ አፍሪካ በግዙፍ ኢኮኖሚዋ አማካኝነት ቀደም ሲል ቀዳሚ የነበረች ቢሆንም የኃይል እጥረት፣ የሎጂስቲክ ችግሮች እና ደካማ ኢንቨስትመንት እንቅፋት ሆነውባታል። በዚህም ምክንያት እ.ኤ.አ በ2026 የኢኮኖሚ ዕድገቷ 1.4 በመቶ ብቻ እንደሚሆን ሪፖርቱ አመልክቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0