አል-ቡርሃን በካርቱም የሚገኘውን ስልታዊ 5ኛ ክፍለ ጦር ብርጌድን ጎበኙ
አል-ቡርሃን በካርቱም የሚገኘውን ስልታዊ 5ኛ ክፍለ ጦር ብርጌድን ጎበኙ
የሱዳን ሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር፤ በመሬት ላይ ያለውን ወታደራዊ ኦፕሬሽን ሂደት ለመገምገም እና በግንባር የተሠማሩ ኃይሎችን የውጊያ ዝግጁነት ለመመዘን የብርጌዱን መምሪያ እንደጎበኙ ምክር ቤቱ አስታውቋል።
የሱዳን ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን በጉብኝታቸው ወቅት፦
የመስክ ሁኔታ ሪፖርቶችን እና የቀጣይ ኦፕሬሽን እቅዶችን በመገምገም ከፍተኛ ወታደራዊ ዲሲፕሊን እና ንቃት አስፈላጊ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
የ5ኛ ብርጌድ አባላት ሀገርን ለመከላከል የከፈሉትን ከፍተኛ መስዋዕትነት በማድነቅ የወታደሮቹ ጀግንነት ለሀገሪቱ መረጋጋት ዋነኛው ዋስትና መሆኑን አረጋግጠዋል።
የጦሩ ሞራል በከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና ቀጣይ የውጊያ ግዳጆችን ለመፈጸም ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ ወታደራዊ ምንጮች ገልጸዋል።
የ5ኛ ብርጌድ ስልታዊ ሚና
ብርጌዱ እ.ኤ.አ በግንቦት 2025 ሠራዊቱ መልሶ በተቆጣጠራቸው ቁልፍ የካርቱም ስፍራዎች የሰፈረ ሲሆን መዲናዋን ከአማጺው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (አርኤስኤፍ) ርዝራዦች ለማጽዳት እየተከናወነ ባለው ወታደራዊ ዘመቻ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
ℹ ጉብኝቱ፤ ከሱዳን ጦር ተከታታይ የጦር ሜዳ ድሎች፤ በተለይም በጥር ወር አጋማሽ በደቡብ ኮርዶፋን ግዛት የዳላንግ ከተማን ከበባ በመስበር የሠራዊቱን የውጊያ ቁመና ካጠናከረ በኋላ የመጣ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X



