ኢኮዋስ ጊኒ ቢሳው ወደ ሕገ-መንግሥታዊ ስርዓት ለመመለስ እየወሰደች ያለውን እርምጃ አደነቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢኮዋስ ጊኒ ቢሳው ወደ ሕገ-መንግሥታዊ ስርዓት ለመመለስ እየወሰደች ያለውን እርምጃ አደነቀ
ኢኮዋስ ጊኒ ቢሳው ወደ ሕገ-መንግሥታዊ ስርዓት ለመመለስ እየወሰደች ያለውን እርምጃ አደነቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.02.2026
ሰብስክራይብ

ኢኮዋስ ጊኒ ቢሳው ወደ ሕገ-መንግሥታዊ ስርዓት ለመመለስ እየወሰደች ያለውን እርምጃ አደነቀ

የጊኒ ቢሳው የሽግግር ግዜ ፕሬዚዳንት ጄኔራል ሆርታ ኢንታ-አ፤ "አካታች የፖለቲካ ምህዳር ለመፍጠር" የተወሰዱ እርምጃዎችን ለምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኢኮዋስ) ሊቀመንበር በደብዳቤ ማሳወቃቸውን ድርጅቱ በመግለጫው አስታውቋል።

የተወሰዱት እርምጃዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

◻ ሁሉንም ወገኖች ያሳተፈ የሽግግር መንግሥት ማቋቋም፣

◻ ከፖለቲከኛው ፈርናንዶ ዲያስ ዳ ኮስታ ቡድን እና ከጊኒ እና ኬፕ ቨርዴ ነፃነት ፓርቲ የተውጣጡ 10 ተወካዮችን በብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት ውስጥ ማሳተፍ፣

◻ ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች መፍታት እና ለዶሚንጎስ ሲሞስ ፔሬራ የተሻለ የእስር ሁኔታን ማመቻቸት፣

◻ የኢኮዋስ ተልዕኮ ከሀገር እንዲወጣ ቀርቦ የነበረውን ጥያቄ ማንሳት።

"ኢኮዋስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሰላማዊ፣ ተዓማኒ እና ወደ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለሚያመራ የሽግግር ሂደት በትብብር እንዲሠሩ ያሳስባል" ሲል መግለጫው አጠቃሏል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0