ኢትዮጵያ በ6 ወር ውስጥ ከግብርና ምርቶች የወጪ ንግድ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ሰበሰበች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በ6 ወር ውስጥ ከግብርና ምርቶች የወጪ ንግድ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ሰበሰበች
ኢትዮጵያ በ6 ወር ውስጥ ከግብርና ምርቶች የወጪ ንግድ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ሰበሰበች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.02.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በ6 ወር ውስጥ ከግብርና ምርቶች የወጪ ንግድ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ሰበሰበች

ገቢው በ2018 የበጀት ዓመት አጋማሽ ከዘርፉ ለማግኘት ታቅዶ ከነበረው 1.9 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ብልጫ እንደታየበት የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የስንዴ ምርት በመኸርና በበጋ መስኖ ከ300 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ደርሶ፤ ኢትዮጵያ ከ4 ዓመት በፊት ለስንዴ ግዢ ታወጣ የነበረውን እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የውጭ ምንዛሪ ማስቀረት መቻሉን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸውን የ6 ወር አፈጻጸም በገመገሙበት ወቅት ገልጸዋል።

ባለፉት 6 ወራት 2.6 ሚሊዮን የዳልጋ ከብቶች ዝርያ በሰው ሠራሽ መንገድ መዳቀሉም ተመላክቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0