የኢትዮጵያ የንፋስ ኃይል የማመንጨት አቅም 504 ሜጋ ዋት ደረሰ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ የንፋስ ኃይል የማመንጨት አቅም 504 ሜጋ ዋት ደረሰ
የኢትዮጵያ የንፋስ ኃይል የማመንጨት አቅም 504 ሜጋ ዋት ደረሰ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.02.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የንፋስ ኃይል የማመንጨት አቅም 504 ሜጋ ዋት ደረሰ

በትናንትናው ዕለት የተመረቀው የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ የመጀመሪያ ምዕራፍ 80 ሜጋ ዋት የማምረት አቅም በመጨመር፤ ከንፋስ የሚገኘውን ኃይል መጠን አሳድጓል ሲሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሸብር ባልቻ ተናግረዋል።

ቀደም ሲል የተሠሩት የአዳማ አንድ እና ሁለት እንዲሁም የአሸጎዳ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች በድምሩ 324 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ፈጥረዋል ተብሏል።

በሂደት ላይ ያለው የአሰላ ኃይል ማመንጫ እንዲሁም አይሻ 2 የመጀመሪያ ምዕራፍ በአጠቃላይ 180 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም እንዳላቸው ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት ዙሪያ የበኩሏን ትልቅ ሚና እየተጫወተች እንደሆነም ዋና ሥራ አስፈፃሚው በንግግራቸው አንስተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0