የአውሮፓ ወታደራዊ አታሼዎች በአስቸኳይ ከኢራን መውጣት አለባቸው - ሕግ አውጪ
16:03 01.02.2026 (የተሻሻለ: 16:04 01.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአውሮፓ ወታደራዊ አታሼዎች በአስቸኳይ ከኢራን መውጣት አለባቸው - ሕግ አውጪ
የኢራን የፓርላማ አባል አሊሬዛ ሳሊሚ፤ "በኤምባሲዎቻችን ውስጥ የሚገኙ የአውሮፓ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች በቶሎ ከሀገሪቱ ግዛት መውጣት አለባቸው። እነሱ አሸባሪዎች ናቸው" ማለታቸውን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ይህ ጥያቄ የኢራን ፓርላማ በዛሬው ዕለት ባሳለፈው ውሳኔ የሁሉንም የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት ወታደራዊ ኃይሎች በይፋ "አሸባሪ ድርጅት" ብሎ መፈረጁን ተከትሎ የመጣ ነው።
እንደ የፓርላማ አፈ ጉባኤው ገለጻ፤ እርምጃው የአውሮፓ ኅብረት ቀደም ብሎ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ዘብ ኃይልን በአሸባሪነት በመፈረጅ ላሳለፈው ውሳኔ የተሰጠ ቀጥተኛ አጸፋዊ ምላሽ ነው።
እነዚህ "አሸባሪ" አታሼዎች በሀገሪቱ እንዲቆዩ መፍቀድ የኢራንን ሕግ ይጥሳል ያሉት ሳሊሚ፤ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፓርላማውን ትዕዛዝ በአስቸኳይ እንዲያስፈጽም አሳስበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X