ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዱባይ ማራቶን በፍጹም የበላይነት አጠናቀቁ
13:49 01.02.2026 (የተሻሻለ: 13:54 01.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዱባይ ማራቶን በፍጹም የበላይነት አጠናቀቁ
በወንዶች ምድብ 3ኛ ደረጃን ይዞ ከገባው ሩዋንዳዊው አትሌት ጆን ሃኪዚማና ውጪ፤ የኢትዮጵያ አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ከ1ኛ እስከ 10ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቀዋል።
አትሌት ንብረት መላክ በወንዶች ምድብ ባለፈው ዓመት የተመዘገበውን ሰዓት በ50 ሰከንድ አሻሽሎ ርቀቱን በ2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ አጠናቋል። በሴቶች ደግሞ አትሌት አንቺንአሉ ደሴ 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በቀዳሚነት ማጠናቀቅ ችላለች፡፡
የዘንድሮውን ጨምሮ የኢትዮጵያ አትሌቶች ለተከታታይ አራት ዓመታት በዱባይ ማራቶን በሁለቱም ምድቦች አሸናፊ መሆን ችለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia
/