ሩሲያ፤ በደህንነት ዋስትና ስም የኔቶ ጦር ዩክሬን ውስጥ እንዲሰፍር አትፈቅድም - የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ፤ በደህንነት ዋስትና ስም የኔቶ ጦር ዩክሬን ውስጥ እንዲሰፍር አትፈቅድም - የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ሩሲያ፤ በደህንነት ዋስትና ስም የኔቶ ጦር ዩክሬን ውስጥ እንዲሰፍር አትፈቅድም - የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.02.2026
ሰብስክራይብ

ሩሲያ፤ በደህንነት ዋስትና ስም የኔቶ ጦር ዩክሬን ውስጥ እንዲሰፍር አትፈቅድም - የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

"የኔቶ አባልነትም ሆነ የውጭ ሀገር ወታደራዊ ኃይል አይኖርም። አንድ የፈረንሳይ ወታደር ‘የኔቶ’ ወይም ‘የአውሮፓ ኅብረት’ ቆብ መልበሱ ልዩነት አይፈጥርም፡፡ የሚቀይረው ነገር የለም። እኛ ከአቋማችን ዝንፍ አላንልም" ሲሉ የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ግሩሽኮ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፤ ውይይት እየተደረገበት ያለው የደህንነት ዋስትና በአሜሪካ ድጋፍ ከበርካታ የአውሮፓ ሀገራት በተለይም ከፈረንሳይ እና ከዩናይትድ ኪንግደም የተውጣጡ ወታደሮች በዩክሬን ውስጥ እንዲሰፍሩ የሚል ሃሳብ እንደሚያካትት ረቡዕ ዕለት ገልጸዋል። ሆኖም ስለድጋፉ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው ምላሽ፤ የኔቶ ጦር በዩክሬን መሠማራት "በፍጹም ተቀባይነት የሌለው" ሃሳብ መሆኑንና ከፍተኛ መካረር እንደሚያስከትል አስጠንቅቋል። መግለጫው ከዩናይትድ ኪንግደም እና ከሌሎች የአውሮፓ ኅብረት ሀገራት የሚመጡ መሰል ሀሳቦች ግጭቱን ለማራዘም የሚደረጉ ቅስቀሳዎች ናቸው ስትል ሩሲያ ቀደም ሲል የሠነዘረችውን ትችት የተከተለ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0